Posted by admin on 2024-05-01 21:36:08 |
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Telegram Visits: 111
ለመጪው የትንሳኤ በዓል የሚያስፈልጉ ነገሮች አስቀድሞ ማዘጋጀት ጠቀሜታው የላቀ ነው!
ተቋማችን ለመጪው የትንሳኤ በዓል ዋዜማና ዕለት የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመሰጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ቢሆንም፤ ለበዓሉ የሚያስፈልጉና በኤሌክትሪክ የሚዘጋጁ ነገሮች ከወዲሁ አስቀድሞ ማዘጋጀት ጠቀሜታው የላቀ ነው፡፡
ለበዓል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከወዲሁ ማዘጋጀት በዋዜማውና በዕለቱ የሚከሰትን የኤሌክትሪክ መቆራረጥና መዋዥቅ ለመቀነስ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም እንገልፃለን፡፡
የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ደግሞ በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ ወረፋ ለማስቀረት ከወዲሁ በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድማችሁ እንድትገዙ /ካርድ እንድትሞሉ/ እናሳስባለን፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን በቤት ውስጥ ሆነ በሥራ ቦታ ጥቅም ላይ የሚውሉ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
እንዲሁም የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓት በተለይ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዜያት መጠቀም የተሻለ አማራጭ መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡